Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ማደራጃ አዋጅን ለማሻሻለ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ማደራጃ አዋጅን ለማሻሻለ እየመከረ ነው።
በውይይቱ እየተደረገ ያለው ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከሀገር አቀፍና ከክልል ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንቶች እና ከክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊዎችና ሌሎች ዘርፉ ከሚመለከታው ኃላፊዎች ጋር መሆኑ ተመላክቷል።
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያና ቁጥጥር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው ÷ ሀገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገው ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ግቡን ሊመታ የሚችለው በንግዱ ብሎም በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ሚናቸውን በአግባቡ ሲወጡ ነው ብለዋል፡፡
የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቱ ለረጅም አመታት ያገለገለ፣ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አብሮ የማይሄድና የንግዱን ማህበረሰብ ብሎም አምራቾችን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ጉድለቶች የሚታዩበት በመሆኑ ማሻሻል አስፈላጊ እንደሆነ አቶ እሸቴ አስፋው ገልፀዋል፡፡
ሚኒስቴር ዴኤታው አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓት ለማስፈን ብሎም የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ኢንጅነር መላኩ እዘዘው በበኩላቸው÷ ረቂቅ አዋጁ 18 አመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ የዘርፉን የአሰራር ማነቆዎች በሚያስወግድ መልኩ ይሻሻል ዘንድ የሚመለከታቸውን የዘርፉ ተዋናዮች ሀሳብ እንዲያካትት ለማረግ በተለያዩ ጊዜያት ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል።
የሀገር አቀፍና ክልል ዘርፍ ማህበራት ፕሬዘዳንቶችና የክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎችም ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማንሳት ለአዋጁ መሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.