ከ300 በላይ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ያቀፈ ምክር ቤት የምሥረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት የምሥረታ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን የእርስ በርስ ቁጥጥርንና አስተዳደር እንዲሁም ዘርፉን በጠንካራ ተቋም የመወከል ዓላማ እንዳለው ታውቋል፡፡
በኮቪድ-19 ምክንያት ከ300 በላይ የሲቪክ ድርጅቶች በምክር ቤቱ ምሥረታ ሂደት የሚሳተፉ ቢሆንም፥ የሚመሠረተው የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት በመላ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ እንደሚያቅፍም ተመልክቷል።
በቅርቡ የተሻሻለው የሲቪል ማኅበራት አዋጅ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት እንዲመሠረት የሚያበረታታ ሲሆን ÷ ይህም ተቋማቱ መብቶቻቸውን እንዲያስከበሩ ያግዛል ተብሏል።
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ተስፋዬ ዳባ የምክር ቤቱ ምሥረታ የሲቪል ማኅበራት በግልጽነት እና በተጠያቂነት ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ያግዛል ብለዋል።
የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች የሠለጠነ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲገነባ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡም ጠይቀዋል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የምክር ቤቱ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት ከተካሄደ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከተመረጠ በኋላ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት በይፋ እንደሚመሠረት ይጠበቃል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!