Fana: At a Speed of Life!

የኮሚሽነሮች ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ስራውን ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በጸደቀው የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1224/2012 መሠረት የኮሚሽነሮች ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ተሰብስቦ ስራውን ጀምሯል፡፡
በዚህ መሠረት የኮሚሽኑን ምክትል ዋና ኮሚሽነር እና የልዩ ልዩ ዘርፍ ጉዳዮች ኮሚሽነሮችን ለመምረጥ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሕዝብ ጥቆማ እንደሚቀበል ታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የልዩ ልዩ ዘርፍ ጉዳዮች ኮሚሽነሮች ማለትም የሴቶችና ሕጻናት መብቶች ጉዳይ፣ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጉዳይ፣ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ጉዳይ፣ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ መብቶች ጉዳይ እንዲሁም የስደተኞች፣ የተፈናቃይ ሰዎችና ሌሎችም ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ የሚጨምር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መመዘኛዎችም
የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች
በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች
ለሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ የሆነ/የሆነች እና በሰብአዊ መብቶች ሥራ ወይም ጥናትና ምርመር አስተዋጽኦ ያደረገ/ያደረገች
የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥትን የሚያከብር/የምታከብር
በሕግ ወይም ተዛማጅነት ባለው ሌላ ሙያ የሰለጠነ/ች ወይም ሰፊ ዕውቀትና ልምድ ያካበተ/ያካበተች
ዕድሜ ከ35 ዓመት በላይ የሆነ/የሆነች
በታታሪነት፣ በታማኝነት፣ እና በሥነ ምግባር በሕዝብ ዘንድ ወይም በአካባቢው ነዋሪዎች ወይም በስራ ባልደረቦች ዘንድ መልካም ስም ያተረፈ/ያተረፈች
ሲሆኑ የዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው በሕዝብ ጥቆማ ከቀረቡት ሰዎች ውስጥ በተቻለ መጠን የልዩ ልዩ ሕብረተሰብ ክፍሎች እና የጾታ ስብጥርን ከግምት በማስገባት መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሟሉ ዕጩዎችን መርጦ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.