በሀገር ግንባታ ውስጥ የወጣቶች ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በሀገር ግንባታ ውስጥ የወጣቶች ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የተዘጋጀው በሀገር ግንባታ ውስጥ የወጣቶች ሚና ላይ ያተኮረው የውይይት መድረክ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ምሁራንን ያካተተ ነው።
በኢትዮጵያ ባሉ ከ1 ሺህ 100 በላይ ከተሞች ምክንያታዊ ወጣትን ለመፍጠር ያለመ ውይይት የተጀመረ ሲሆን÷ በውይይቶቹ የምሁራንን ተሳትፎ ለመጨመር በማለም ነው ይህ የምሁራን ውይይት እየተካሄደ የሚገኘው።
“በሀገረ መንግሥት እና ብሔረ መንግሥት ግንባታ የወጣቶች ሚና ” በሚል ርዕስነው ውይይቱ እየተካሄደ ያለው።
በተለያዩ ከተሞች በሚካሄደው የወጣቶች ውይይት ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን እንደሚደርስ በመድረኩ መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!