በምስራቅ ሸዋ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የተገነባው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በ20 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ‘ኢፈ ሊበን’ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምርቃ ስነስርዓቱ ላይ መልዕክት ባስተላለፉት መልዕክት÷በሀገሪቱ በቀጣይም ጠንካራ የስራ ባህልና ቁጠባ ለመፍጠር፣ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር እና እውቀትና የቴክኖሎጂን ለማስፋፋት በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽታያቸውም በክልላችን ብሎም በሀገራችን የሚገነቧቸው ትምህርት ቤቶች እንዚህን ያገናዘበና በትውልዱ ልብ ውስጥ የሚቀር ስራ በመስራታቸው የትውልድ እናት መሆናቸውን አሳይተዋል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ሽመልስ አያይዘውምጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጽሀፍን ሽያጭ ገቢ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲውል በመስጠታቸው ከፍተኛ ምስጋና ይባቸዋል ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጩቋላ ወረዳ ጎንጎ ቀበሌ ለምረቃ የበቃው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ አንድ ዓመት የወሰደ ሲሆን በዚህ ዓመት 220 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል።
በክልሉ የዛሬውን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ፣ በምዕራብ ሐረርጌና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ወጪ የተገነቡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ ገብተዋል።
በተጨማሪም በተያዘው ዓመት በክልሉ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ወለጋና ጅማ ዞኖች በጽህፈት ቤቱ አማካኝነት ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ ታውቋል።
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች ረጅም ርቀት ተጉዘው የሚማሩ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የማስቻልና የትምህርት ተደራሽነትን የማስፋት ዓላማ ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም ጽህፈት ቤቱ ትምህርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለአካባቢው ማኅበረሰብ እያስረከበ መሆኑ ተገልጿል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!