ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከሚገኙ አርሶአደሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከሚገኙ አርሶአደሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የተካሄደው “የተቀናጀ የለውጥ አመራር ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል መሆኑም ተመላክቷል።
በውይይቱ ወቅት አርሶአደሮቹ አዲስ አበባ በእጥፍ እንድትሰፋ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ተገቢውን ክብር እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሳናገኝ ስንበደል ቆይተናል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም አሁንም በአካባቢያችን መሰረተ ልማት የለምና ትኩረት ይሰጠን፣ ስማችን የሚያጠፉትን አስቁሙልን” ሲሉ መጠየቃቸው ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን በማልማት እና በማሳደግ ስራው ላይ አርሶአደሩን አካታች ባደረገ እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን በሚያረጋገጥ አግባብ መሆን እንዳለበት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ወይዘሮ አዳነች በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።
በውይይቱ እየተሰራ ያለውን ስራ፣ የወደፊት የአሰራር አቅጣጫ እና አተገባበር የአርሶ አደሩን ችግር እና ቅሬታ የሚፈታ እንዲሆን መግባባት ላይ መደረሱም ተመላክቷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!