Fana: At a Speed of Life!

ከሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሀረሪና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ አመራሮች ስልጠና እየተሠጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ከሀረሪና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ አመራሮች የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተጀመረ።
የፌደራል የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ያዘጋጀው የስልጠና መድረክ በ2ኛው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስተግበሪያ ሰነዶችና ላይ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ለማሳደግ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
በስልጠናው ከሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ከሀረሪና ድሬዳዋ አስተዳደር የተውጣጡ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ተሳታፊ መሆናቸው ነው የተገለጸው።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ÷ በከተሞች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን አግባቡ ተግባራዊ ማድረግ በከተሞች ድህነትን በመቀነስ በኩል ከፍተኛ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቱ የታለመለትን ግብ አንዲመታ በትጋት ሊሰሩ ይገባልም ነው ያሉት ።
አያይዘውም ከድህነት በታች ኑሮ የሚገፉ የከተማ ነዋሪዎችን ኑሮ ለመቀየር የክልሉ መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በክልሉ ስድስት ከተሞች የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመቅረፅ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የፌደራል የከተሞች የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ በሀገሪቱ በተተገበረው የሴፍቲኔት ፕሮግራም ባለፉት አመታት በአካባቢ ጥበቃም ሆነ በቀጥታ የልማት ስራዎች ከ600 ሺህ ላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በፕሮጀክቱ ትግበራ ከተመዘገበው ውጤት በመነሳት 72 ከተሞችን ያካታተው ሁለተኛው ዙር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ወደ ትግበራ መግባቱንም ጠቅሰዋል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው የስልጠና መድረክ ላይ በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ፣ የፕሮጀክቱ ማስተግበሪያ ማንዋል እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.