Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ ቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የሥራ ሂደት ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አፈጻጸም እንዲኖራቸው የሚያስችል ሥልጠና መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተባበሩት መንግስታት በጎ ፍቃደኝነት ተቋም ጋር በመተባበር በቦርዱ የክልል የምርጫ ጽህፈት ቤቶች የሚሠሩ የተመድ በጎ ፈቃደኞች የተዘጋጀ ሥልጠና ዛሬ አስጀምሯል።
ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ሥልጠና የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተገኝተው አስጀምረዋል።
ሥልጠናው የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ላይ የሚኖረውን የሥራ ሂደት ቀልጣፋና ዘመናዊ አፈጻጸም እንዲኖረው ለማስቻል ታስቦ ከተባበሩት መንግስታት በጎ ፍቃደኝነት ተቋም ጋር በመተባበር በጎ ፍቃደኞች በመመልመል የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫ ከዋና አገራዊ ሁነቶች አንዱ መሆኑን አውስተው÷ ለዚህም የጠንካራ ተቋም መኖር ወሳኝ እንደሆነ እና ተቋምም ጠንካራ ለማድረግ በብቁ ባለሞያዎች ማደራጀት ትልቁ አቅም እንደሆነ ገልጸዋል።
ዛሬ የተጀመረው ሥልጠና በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሁሉም ማኅበረሰብ ክፍሎች ድምፅ ዋጋ እንዲኖረው ለማስቻል ለምናደርገው ከፍተኛ ጥረት ያለው ሚና ትልቅ ነው ብለዋል።
ታማኝነትን ማረጋገጥ የሚቻለው ገለልተኛ በመሆን ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ አቅም በመፍጠር ጭምር ነው ያሉት ወይዘሪት ብርቱካን÷አቅም ለመፍጠር ቦርዱ ለሚያደርገው ጥረት የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት እያደረገ ያለውን እገዛ አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት በጎ ፍቃደኞች አስተባባሪ የሆኑት ሰላማዊት ፅጌ በበኩላቸው÷የበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት ለመልካም ለውጦች፣ ለድኅነት ቅነሳ፣ ለሥርዓተ ጾታ እኩልነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለዴሞክራሲ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው÷ ዛሬ የተጀመረው ሥልጠና ዋና ዓላማም እሱ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሥልጠናውም የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ እና የአፈጻጸም ሂደት፣ የሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት፣ ምርጫ እና ሥርዓተ ጾታ፣ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሂደት፣ የምርጫ ጣቢያዎች እና የድምፅ ቆጠራ ሥርዓት ሂደት እንዲሁም ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥልጠናው ትኩረት ከሚያደርግባቸው አጀንዳዎች ውስጥ መካተታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.