Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የመድሀኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እጥረን ለመቅረፉ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የሚመረምረው ቦርድ በሁለተኛው ዙር የመስክ ምልከታው ግኝቶች ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
መርማሪ ቦርዱ የተወያየው ከጤና ሚንስቴር እንዲሁም ከሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ሲሆን፤ በህግ ማስከበር ዘመቻው የጤና ተቋማት እያደረጉ ባሉት ሰብኣዊ ድጋፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ነበር፡፡
መርማሪ ቦርዱ በሁለተኛው ዙር የመስክ ምልከታ ሽሬ እንዳስላሴ፣ መቀሌ፣ አዲግራት፣ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ መርሳን እና ደሴ ሆስፒታሎችን መጎብኘቱ ተጠቁሟል።
በመስክ ምልከታው በየሆስፒታሎቹ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ለምርኮኞቹ ተገቢው የህክምና አገልግሎት እየተደረገላቸው ያለ መሆኑን የመርማሪ ቦርዱ አባላት ገለፀዋል።
በመሆኑም በየሆስፒታሎች አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አመራሮች፣ ሰራተኞችና የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም የአከባቢው ማህበረሰብ ላደረጉት ሰብኣዊ ድጋፍ ምስጋና የሚገባቸው መሆኑንም ቦርዱ አስረድቷል።
በሌላ በኩል በአንዳንድ ሆስፒታሎች የመድሀኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እጥረት እየገጠመ መሆኑን የገለጸው ቦርዱ የጤና ሚንስቴርን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም አሳስቧል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመድሀኒት እጥረቱን ለመቅረፍ ችግሩ ለታየባቸው ሆስፒታሎች እየደረሰ መሆኑን በመግለጽ በሪፓርቱ ላይ የተጠቀሱትን እጥረቶችን በመፈተሽ ማስተካከል እንደሚገባም ገልፀዋል።
የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ በበኩላቸው መርማሪ ቦርዱ በየሆስፒታሎቹ ያሉትን ተጨባጭ ሁኔታዎች ያየበት ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በጤና ሚኒስቴር በኩል የታዩትን እጥረቶች ለማሟላት በፍጥነት የተሄደበት ርቀት የሚያስመሰግን መሆኑን መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ የጤና ሚኒስቴር እያደረገ ስላለው ጥረት አመስግነው ክትትሉን አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዲሟሉ ጠይቀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.