በባህርዳር የታንኳ ቀዘፋ ውድድር ትርኢት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀልባና የታንኳ ቀዘፋ ውድድር ትርኢት በባህርዳር ከተማ “ጥርን በባህር ዳር” በሚል መሪ ቃል ተካሄደ።
በስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሙሉቀን አዳነ ፣ የባህር ዳር ከተማ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዬ አለባቸው እንዲሁም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም፣ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አብርሃም አሰፋ ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ጥምቀትን በአማራ ክልል ለማክበር ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሃገር የመጡ እንግዶች፣ የባህር ዳርና አካባቢዋ ነዋሪዎች ታድመዋል።
የትርኢቱ ዋና ዓላማ ባህር ዳርን የጥር ወቅት የጎብኚዎች መለያና መዳረሻ ከተማ ማድረግ ሲሆን እየተቀዛቀዘ የመጣውን የታንኳ ቀዘፋ መልሶ ለማነቃቃትና የጥምቀት በዓላትን በጎንደርና በተለያዩ አካባቢዎች ሲያከብሩ ቆይተው የተመለሱ የተለያዩ እንግዶችን ቆይታቸውን ባህር ዳር ላይ ለማድረግ ታስቦ በየአመቱ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቀሟል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!