በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ መኪና በየከይት ቀበሌ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ከ 40 አካባቢ በመገልበጡ የደረሰ ነው ተብሏ፡፡
በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አራት ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በሉማሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ከአዋበል ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡