የመቀሌ ከተማን ሠላም ለማስጠበቅ ከ400 በላይ ነባር የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የመቀሌ ከተማን ነዋሪ ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዙ ከ400 በላይ ነባር የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል ሃላፊ ኢንስፔክተር ሠለሞን ገብረመድህን ለኢዜአ እንደገለጹት ወደ ስራቸው የተመለሱት በተደረላቸው ጥሪ መሰረት ቀደም ሲል በከተማው ከነበሩት ከ800 በላይ የፖሊስ አባላት መካከል ነው።
ወንጀልን በመከላከል የከተማዋን ነዋሪ ህዝብ ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የፖሊስ አባላቱ መደበኛ ስራቸው መጀመራቸውን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በክፍለ ከተማ ደረጃም የፖሊስ አባላትን የማደራጀት እየተከናወነ መሆኑን ኢንስፔክተር ሠለሞን አስረድተዋል።
ህብረተሰቡ ሠላምና ፀጥታውን በማስጠበቅ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ያመለከቱት ኢንስፔክተር ሠለሞን በቀጣይም በቀበሌ ደረጃ የኮሚኒቲ ፖሊስ የማደራጀት ስራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
በከተማ ደረጃ ወንጀሎችን የመከላከል ስራ መቀጠሉን ገልጸው በእስካሁኑ ሂደትም ልዩ ልዩ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ45 ግለሰቦች መያዛቸውንና ጉዳያቸው ተጠርቶ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም አስታውቀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!