በትግራይ ሕዝቡ ማምረትና የራሱን ገቢ ማመንጨት እስከሚጀምር ሠብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ እንደሚቀጥል ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ እየተደረገ ያለው የሠብዓዊ ድጋፍ ሕዝቡ የራሱን ምርት ማምረት እስከሚጀምር እንደሚቀጥል ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽነር ምትኩ ካሣ በመቐለ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት እንዳስታወቁት በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት ላጋጠማቸው ወገኞች የሚሰጠው ሰብዓዊ ድጋፍ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉንና መንግስት ለዚህ በቂ አቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉን ለማዳረስ 88 ጣቢያዎች መቋቋማቸውንና እስካሁንም በ82 ጣቢያዎች ሰብዓዊ ድጋፍ መከፋፈሉን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነር ምትኩ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አንዳንድ አካባቢዎች በወታደራዊ እጀባ ጭምር ሰብዓዊ ድጋፍ እየደረሰ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሠብዓዊ ድጋፉ በትግራይ ክልል ሰባት ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች እየተዳረሰ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በተቀሩት ስድስት ጣቢያዎች ለመድረስም የምግብ ቁሳቁሶች ማጓጓዝ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ሕዝቡ ማምረት እስከሚጀምርና የራሱን ገቢ ማመንጨት እስኪችል ድረስ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!