Fana: At a Speed of Life!

ፌሌክስ ሺሴኬዲ ከራማፎሳ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ተረክበዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ ከተሰናባቹ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪይል ራማፎሳ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ተረክበዋል፡፡

ተሰናባቹ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ለአዲሱ ሊቀመንበር የእንኳን ደስ ያሎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

እንዲሁም የአፍሪካ ህብረትን ሰንደቅ አላማ በቨርቹዋል በሚካሄደው ጉባዔ ላይ በተምሳሌትነት ሰጥዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን የተረከቡት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲም ንግግር አድርገዋል፡፡

ተሰናባቹ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት 34ኛውን መደበኛ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች እና የርዕሳነ ብሔራት ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

መደበኛ ስብሰባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲካሄድ መወሰኑንም ገልጸዋል፡፡

ራማፎሳ ኮሮና ቫይረስ ተከሰተ በኋላ አህጉሪቷ ወረርሽኙን ለመከላከል እያደረገች የምትገኘው ጥረት አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም አህጉሪቷ ወረርሽኙን በምትከላከልበት በዚህ ወቅት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠናን ዕውን ማድረጓን እንደስኬት አንስተዋል፡፡

የንግድ ቀጠናው ዕውን መሆኑም ለአህጉሪቷ ዕድገት፣ ልማትና ብልጽግናን እንደሚያመጣ ነው የገለጹት፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.