Fana: At a Speed of Life!

የላይኛው ጉደር መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመስኖ ልማት ኮሚሽን ባለቤትነት የላይኛው ጉደር መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ እየተካሄደ ነው።

ፕሮጀክቱ በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር በቶኬ ኩታዬ እና አምቦ ዙሪያ ወረዳዎች በዘጠኝ ቀበሌዎች  በሁለት ክፍል ተከፍሎ ግንባታው እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ የግንባታ  ለሶስት ዓመታት የሚቆይ  ሲሆን÷የግድቡ ውሃ የመያዝ  አቅም 56 ሚሊየን ሜትር ኩብ  መሆኑም ተመላክቷል።

የግድቡ ርዝመት 277 ሜትር ሲሆን ከፍታው ደግሞ 40 ነጥብ 5 ሜትር መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 12 ሺህ 137 አርሶአደሮች በቶኬ ኩታዬና አምቦ ዙሪያ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ  ነዋሪዎችን የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ፕሮጀክቱ በእስፕሪንክለር መስኖ አውታር ግንባታ 5 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት  የሚችል ነውም ነው የተባለው፡፡

በግድቡ ግንባታ እስካሁን ለ387 የአካባቢው ህብረተሰብ የስራ እድል መፈጠሩን ከውሃና መስኖ ኢነርጂ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ብዙነህ ቶልቻ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.