Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በ6 ወራት ውስጥ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6 ወራት ውስጥ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ ማድረግ መቻሉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

ከቴምብር ሽያጭ 7 ሚሊየን 91 ሺህ 595 ብር እና ከአገልግሎት ክፍያ 4 ሚሊየን 424 ሺህ 977 ብር መገኘቱን የመስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ ገልጸዋል፡፡

በድምሩ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የተገኘ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ገቢ መገኘቱን አቶ ዓለምሸት ገልጸዋል፡፡

አቶ ዓለምሸት ምህረቴ እንደገለፁት በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት ውስጥ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ 266 ሺህ 628 ተገልጋዮች መስተናገዳቸውን ነው ያስረዱት፡

መስሪያ ቤቱ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ውክልና መስጠትና መሻር፣ ትርጉም ማረጋገጥ፣ የትምህርትና ስልጠና ውል፣ የኑዛዜ መስጠትና መሻር፣ ሰነድ ማገናዘብ/ቅጅ ማመሳከር የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ለአገልግሎቱ መሳለጥ ተገልጋዩ ህብረተሰብ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ መገኘት እንዳለበት በየጊዜው ሁሉም ዐቃቤ ሕግ ባገኘው አጋጣሚ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ግንዛቤ ለፈጥር እንደሚገባውም ከክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.