ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሌ/ ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዘሙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዝመዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9)እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደርን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት ያራዘሙት፡፡
#PMOEthiopia