ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቡሩንዱ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር የሃገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ከውይይታቸው በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫም የሃገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም በሶማሊያ እያደረገች ላለው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው በቡሩንዲ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዴሞክራሲን ለማጠናከር እየተሰራ ያለውን ስራ እና ቡሩንዲ በሶማሊያ እና በመካከለኛው አፍሪካ በሰላም ማስከበር ሂደት የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!