የጤና ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በረቂቅ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የጤና ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በረቂቅ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የጤና አዋጅ አሁን ላይ በጤና አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶች የሚያስተካክልና አጠቃላይ የጤና ስርዓቱን የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
ከዚያም ባለፈ ቀደም ሲል በወጡ የጤና አዋጆች ያልተካተቱ አንዳንድ የጤና አገልግሎቶችን ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ያስችላል ተብሏል።
በአዋጁ ረቂቅ ዝግጅት የመጨረሻ የውይይት ሂደት ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ ረቂቅ አዋጁን ለማዘጋጀት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን የማወያየትና የማማከር ስራዎችን ከመስራት ጀምሮ በርካታ ሂደቶችን እንዳለፈ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ረቂቅ አዋጁ ቀደም ሲል በአዋጅ ያልተካተቱ የጤና አገልግሎቶችን ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው የሚያስችል አልፎም አጠቃላይ የጤና ስርዓቱን ሊያጠናክሩ የሚችሉ አዳዲስ ድንጋጌዎችንም አካቷል ብለዋል።
አዋጁ ከሌሎች የአገሪቷ ህጎችና አዋጆች ጋር እየተመሳከረ እንደተዘጋጀና በአሁኑ የረቂቅ አዋጅ ውይይትም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው በቡድን ውይይት እየተደረገ ሲሆን ከውይይቱም አዳዲስ ምክረ ሀሳቦችና የውሳኔ ሀሳቦችምእንደሚጠበቁ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!