Fana: At a Speed of Life!

ለተመድ የልማት ግቦች ስኬት የድንበር አካባቢ እድገትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የድንበር አካባቢ ልማትን በማስፋት የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማትን ግቦችን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ተገለፀ፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በቱርካና ክልል ሎድዋር የአፍሪካ የድንበር አካባቢ ልማት ማዕከል ምስረታ ላይ ባደረጉት ንግግር የድንበር አካባቢን ሠላም ለማስጠበቅ፣ ልማት ለማረጋገጥ አካባቢና አገር በቀል ልምዶችንና እውቀቶችን  መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ ያሉ ህዝቦችን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እና የአውሮፓ ህብረት የጀመሩት ፕሮጀክት እንዲሳካ በኢትዮጵያ በኩል ድጋፍ እንደሚደረግ አምባሳደር መለስ ተናግረዋል፡፡

የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ለዘመናት የልማት ተጠቃሚ ባልሆኑ ጠረፍ አካባቢዎች የሚካሄደው ልማት ለክፍለ-አህጉራዊ ውህደት ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

የኬንያ ዲቮሊዩሽን ሚኒስትር ዩጂን ዋማልዋ በበኩላቸው የድንበር አካባቢ ህዝቦች ፈተናዎች ድህነትና የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያና ኬንያ ሞያሌ-መርሣቤት ኮሪደር መልማት ለአካባቢው ሠላምና ደህንነት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ መጥቀሳቸውንም ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.