Fana: At a Speed of Life!

ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ካናል ፕላስ በቅርቡ በኢትዮጵያ በተለያዩ የቴሌቪዥን ቻናሎች ለተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለዚህ ይረዳው ዘንድም ከኢዩቴልሳት ጋር ከወራት በፊት ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፥ ስርጭቶቹንም በኢዩቴልሳት 7ሲ ቻናሎች ላይ ያስተላልፋል ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይም ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች በመደበኛና በከፍተኛ ጥራት የሚቀርቡ 50 ያህል ቻናሎችን ለማድረስ ዝግጅት ማጠናቀቁን የዳታ አክሲስ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ይህም የኢትዮጵያን ብሮድካስት ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እና ቻናሉ ከሰሃራ በታች ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት ያግዘዋል ተብሏል፡፡

ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ይሆናል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.