Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ በማርዋዲ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ በማርዋዲ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እንዲሁም በመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከት መምከራቸው ታውቋል፡፡
በዚህ ወቅት አምባሳደሯ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የሃሰት መረጃ ዜና ዘመቻ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ከእውነት የራቁ እና የሚሰራጩን የሃሰት መረጃዎችን እንዲከላከሉ አሳስበዋል ፡፡
ተማሪዎቹ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የሃሰት ዜና ዘመቻ ለመከላከል ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም በውይይቱ በተማሪዎች የተነሱ አካዳሚክ እና ተዛማጅ ጉዳዮችን መፍታት እና መለየት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በመጨረሻም ተማሪዎቹ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከኤንባሲው ያገኘነው ዜና ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.