የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተኑ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የነበረውን ስነ ልቦናዊ ጫና ታሳቢ ባደረገ መልኩ ይወሰናል – ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የነበረውን ስነ ልቦናዊ ጫና ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚወሰን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
የዘንድሮው ፈተና ሳይሰረቅ መሰጠቱን ያነሳው ሚኒስቴሩ፥ ከ358 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሰዳቸውንም ገልጿል፡፡
ፈተናው የጸጥታ ችግር በነበረባቸው የትግራይና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞንን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ ተሰጥቷል፡፡
የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ካለባቸው የስነ ልቦና ጫና አንጻርም የውጤት ምዘና ላይ ሁኔታው ታሳቢ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የዘንድሮው ተፈታኞች የትምህርት ዘመናቸው ሳይባክን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ውጤት በቅርቡ ይገለጻልም ነው የተባለው፡፡
በአላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!