Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ የለማ ከ130 ሺህ ሄክታር በላይ የስንዴ ምርት መሰብሰብ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ የለማ ከ130 ሺህ ሄክታር በላይ የስንዴ ምርት የመሰብሰብ ስራ የተጀመረ ሲሆን በአማራ ክልል በመስኖ ልማት የተሸፈነው ሰንዴ ተሰፋ ሰጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት እርሻው በሁለቱም ክልሎች የተሻለ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የየክልሎቹ የስራ ሃላፊዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የሰንዴ ፕሮጀክት አሰተባባሪ አቶ ጣሃ ሙሜ እንደተናገሩት ÷በተያዘው ዓመት በክልሉ160 ሺህ ሄክታር በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ከ130 ሺህ በላይ ሄክታሩን ማሳካት ተችሏል።
በዚህም በመጀመሪው ዙር የተዘራውን ስንዴ የመስብሰብ ስራ ተጀምሯል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ያጋጠሙ ችግሮችን በመቅረፍም በሁለተኛው ዙር የመስኖ ልማት የተሻለ ምርት ለማግኝት ይሰራል ብለዋል።
በተመሳሳይ በተያዘው ዓመት በአማራ ክልል 17 ሺህ 731 ሄክታር የመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ 13 ሺህ ሄክታር በዘር ተሸፍኗል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተሰፋሁን መንግስቴ እንደተናገሩት አሁን ላይ የተዘራው ሰንዴ ተስፋ ሰጭ ነው፡፡
በሌላ በኩል ለበጋ ስንዴ መስኖ ልማቱ የምርጥ ዘር አቅርቦት ችግር የነበረ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የተሻለ ምርት ለማግኘት ይሰራል ብለዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.