Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ የኮቪድ-19 ክትባትን በይፋ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ ጤና ጣቢያ በመገኘት የኮቪድ-19 ክትባትን በይፋ አስጀምረዋል።

ወይዘሮ አዳነች በዚሁ ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጀምሮ ቫይረሱን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ግንባር ቀደም ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የኮቪድ-19 ክትባቱም በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ የገለፁት ምክትል ከንቲባዋ ህብረተሰቡ ክትባቱ እስከሚደርሰው ድረስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው በኮቫክስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በእድሜ ጭምር ለበሽታው አጋላጭ በሆነ የጤና ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሠጥ ገልጸዋል፡፡

በሃብታሙ ተክለስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.