የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርዓ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በታዋቂና ከያኒ አለምጸሃይ ወዳጆ የተመሰረተው ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል ላለፉት 20 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ በኪነ-ጥበብና በትምህርት ላይ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።
ማዕከሉ በተለያዩ የአለምአገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጰያውያን የአገራቸውን ባህልና ቋንቋ በማስተዋወቅ በኩልም ጉልህ ሚና ተጫውቷል።
በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዛሬ 117 ዓመት ተገንብቶ በቅርስነት የተመዘገበውን የቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤልን መኖሪያ ቤት ለጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል አስረክቧል።
እየተካሄደ ያለው መርሃ ግብርም ማዕከሉን ማስተዋወቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
በመርሃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!