Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ በደቡብ ሱዳን ከተሰማሩ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቆች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ በደቡብ ሱዳን ጁባ ፣ ቦር እና ያምቢዮ አካባቢዎች ከተሰማሩ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቆች ጋር ተወያዩ፡፡

ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ በደቡብ ሱዳን ከተሰማራው ከ12ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮለኔል ግርማ ለታ ፣ ከ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ  መለስ መንግስቴ ፣ ከ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮለኔል መለስ ይግዛውና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አስተባባሪ ኮለኔል ሙላው በየነ ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዝግጅነት ዙሪያ መክረዋል ፡፡

በዚህ ወቅትም የተከናወነውን የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ እንዲሁም የኢትዮጵያን ስምና ዝና አስጠብቆ ግዳጅን በውጤታማነት ከመፈፀም አንፃር ሰራዊቱ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ትኩረት ሰጥተዋል ተወያይተዋል፡፡

ሌተናል ኮለኔል ፀጋዬ አብራሃ ጨምሮ የውይይቱ ተሳታፊዎች በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት አንመለስም በማለት ጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ግርግር በመፍጠር የጁንታውን ተልዕኮ ለማስፈፀም የሞከሩ 15 ግለሰቦችን ድርጊት ኮንነዋል ፡፡

እነዚህ አባላት ቀን ከለሊት ያውም በጎረቤት ሀገር ላይ የኢትዮጵያን ስምና ዝና አስጠብቆ ለሰላም የቆመውን ኃይል የማይወክሉ መሆናቸውን ማንሳታቸውን ከሰራዊቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጄኔራል መኮንኑ በሰላም ማስከበር ላይ የተሰማራው ሰራዊት ዛሬም እንደ ትላንቱ የኢትዮጵያን ዓርማ ይዘው ታሪክ እንደሰሩት አባቶቹ ፣ አደራውን ተወጥቶ አኩሪ ገድሉን ለትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.