በአማራ ክልል በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 30 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡
አደጋው በወረዳው በቤዛ ብዙሃን ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡሃች በተባለ ቦታ በዛሬው ዕለት ማለዳ 1 ሰዓት ላይ ነው የደረሰው፡፡
በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ 6 ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ ባህር ዳር መላካቸው ተገልጿል፡፡
የትራፊክ አደጋው ከጎንደር ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ባስና ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ተነስቶ ወደ ወይን ውሃ ይጓዝ የነበረ ቅጥቅጥ አይሲዙ መኪና በመጋጨታቸው የደረሰ መሆኑን ከሞጣ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!