Fana: At a Speed of Life!

በእነ ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ በእነ ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲ ነጮ) ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡

ክሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብርና ህገ መንግስት ጉዳዮች የወንጀል ችሎት መስርቷል፡፡

ክስ ከተመሰረተባቸው 21 ተከሳሾች ውስጥ ዛሬ በችሎት ተገኝተው ክሱ የደረሳቸው፥ 1ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ፤ ሳይበር ዋና መምሪያ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ፣ 2ኛ የመከላከያ ሚኒስቴር ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሲስተም መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ገብረህይወት ደስታ፣ 3ኛ የመከላከያ የግንኙነት መሳሪያ ሪፈራል ቡድን መሪ የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ዩሃንስ በቀለ፣ ሻምበል ብርሃነ ግብሩ፣ ሻምበል ሃይለስላሴ ግርማይ፣ ሻለቃ ገብረእግዛብሄር ግርማይ እና ኮሎኔል ዘነበ ታመነ ናቸው።
ቀሪዎቹ ተከሳሾች በችሎት ያልተገኙ ሲሆን የዐቃቤ ህግ ክስ እንዲደርሳቸው እንዲመለከቱት ተደርጓል።

ተጠርጣሪዎቹ ላይ የመከላከያ ሬዲዮ ግንኙነትን በማቋረጥ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ጦር ላይ ጥቃት እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው ምርመራ ሲከናወንባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.