የጃፓኑ ማሩያማ ኮሙቴን ኩባንያ በኢትዮጵያ በግንባታው ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማራው የጃፓኑ ማሩያማ ኮሙቴን ኩባንያ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡
አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ከኩባንያው ሊቀ መንበር ታዪዞ ያማሞቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም አምባሳደር ካሳ ለሊቀ መንበሩ በኢትዮጵያ በሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
በተለይም በግንባታው ዘርፍ በሃገሪቱ ከተያዘው የ10 አመት የትራንስፖርት እቅድ ጋር በተያያዘ ገልጸውላቸዋል፡፡
የማሩያማ ኮሙቴን ሊቀ መንበር ታዪዞ ያማሞቶ በበኩላቸው ኩባንያቸው በኢትዮጵያ በዘርፉ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በዘርፉ በተለይም የግንባታ ማሽነሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማቅረብና በመሰረት ግንባታ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ኩባንያቸው ለኢትዮጵያውያን በዘርፉ ስልጠና በመስጠት የቴክኖሎጅ እውቀትን ለማስተላለፍ ዝግጁ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!