Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በኢፋ ቦሩ ፕሮጄክት እየተሰሩ ካሉ ትምህርት ቤቶች የ44 ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በኢፋ ቦሩ ፕሮጄክት እየተሰሩ ካሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የ44 ትምህርት ቤቶት ግንባታ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት÷ግንባታቸው የተጠናቀቀው 44 ትምህርት ቤቶች ለመጀመሪያ ዙር ምርቃት ደርሰዋል፡፡
ሰባት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በኢፋ ቦሩ ፕሮጄክት በግንባታ ላይ ያሉ ትምህርት ቤቶችም በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው ተጠናቆ ለሁለተኛ ዙር ምርቃት ይደርሳሉ መባሉን የአቶ አዲሱ አረጋን ማህበራዊ ትስስር ጠቅሶ ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
በክልሉ በተያዘው የበጀት ዓመት በኢፋ ቦሩ ፕሮጄክት 100 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 40 ልዩ ትምሀርት ቤቶች እና 7 አዳሪ ልዩ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት እቅድ ተይዞ እንደነበር ይታወሳል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.