የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፉን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፉን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን አስታወቁ፡፡
ለዚህም በዘርፉ የኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ ትኩረት እየተደረገ መሆኑን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትራንስፖርት ፖሊሲ፣ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ሎጅስቲከስ ፖሊሲ፣ ብሔራዊ ሎጅስቲክስ ስትራቴጂ እና ሞተር-አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጂ መነደፉን ጠቁመዋል፡፡
በአጠቃካይ 2 ሺህ 721 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ የተገነባ ሲሆን፥ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት እና ወደ ውጭ የመላክ የሎጂስቲክስ ሂደት ከ17 ሚሊየን ቶን በላይ ደርሷልም ነው ያሉት፡፡
ይህም በኢትዮጵያ የንግድ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ተደርጎ እንደሚወሰድ አውስተዋል፡፡
የመርከቦች የወደብ ቆይታ ጊዜ ከ40 ቀናት ወደ 12 ነጥብ 75 ቀናት መቀነሱንም ጠቅሰዋል፡፡
ከንግድ አና ሎጅስቲክስ ፍሰት መሻሻል ጋር በተያያዘም የኢትዮ-ኬንያ አንድ ማቆሚያ ድንበር መተላለፊያ መከፈቱንም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ከ26 በላይ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ለህዝብ መተዋወቃቸውን ጠቅሰው፥ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ትኬት ስርዓት መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!