አመርቂ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የመከላከያ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርዓት ተከናወነ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የማዕረግ የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ እና አመርቂ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የመምሪያው አመራሮች እና አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነስርዓት አከናወነ፡፡
በማዕረግ ማልበስ ስነስርዓቱ ላይ በመከላከያ ስራዊት የሰራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡
ማዕረጉ ከምክትል አስር አለቃ እስከ ሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ ያሉ አጠቃላይ ቁጥራቸው 39 ለሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት የተሰጠ መሆነቡን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!