Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 138 የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 138 የቀበሌ መኖሪያ ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች አስተላልፈዋል።

ወይዘሮ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ በህገወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ ቤት ለሚገባቸው ነዋሪዎች እያስተላለፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በቀጣይም በከተማዋ ፍትሃዊነት እንዲሰፍን እና ሁሉም እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.