Fana: At a Speed of Life!

በግብርና ዘርፍ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ – የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በግብርና ዘርፍ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት እና በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ ጉልህ ሚና ያላቸው የኢኮኖሚ ዘርፎችን በመለየት ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በ2014 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ዓመት ውይይት ላይ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በግብርና ዘርፍ እየተተገበሩ የሚገኙትን ተግባራት ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

በተለይም በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው እንቅስቃሴ የምግብ ፍላጎትን በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ ምርት ለማሟላት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

በዚህም የግብርና ግብዓት እና አገልግሎት አቅርቦትን ተደራሽነት የማጎልበት፣ በግብርና አምራቾችና ሸማቾች መካከል የጠበቀ የገበያ ትሳስር የመፍጠር ፣ የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት በግብርና ምርምርና ጥናት፣ በመስኖ ልማት ተሳትፎ የማሳደግ እንዲሁም ግብርና ተኮር የፋይናንስ አገልግሎትን የማጎልበት ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመስኖ ልማት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በዓመት ሁለት ጊዜ እና ከዚያ በላይ ለማምረት የሚያስችሉ ተግባርት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በማምረቻው ዘርፍ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለውጭ ገበያ የሚውሉ እና የገቢ ምርቶችን የሚተኩ አምራቾችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ውጤታማ አሰራሮች እየተተገተበሩ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.