Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተናጥል የተኩስ አቁም አዋጅ ተሰፋ ሰጪ እርምጃ መሆኑን ሩሲያ ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተናጥል የተኩስ አቁም አዋጅ ተሰፋ ሰጪ እርምጃ ነው መሆኑን ሩሲያ ገለጸች።
የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በትግራይ ክልል ተግባራዊ ያደረገው የተናጥል የተኩስ አቁም አዋጅ በክልሉ ላይ ለውጥ ለማምጣት ተስፋ ሰጪ እርምጃ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደሩ በሰጡት ወርሃዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ÷ የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ እያደረገ ላለው ከፍተኛ መጠን ላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትም ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉበት መንገድ ሊመቻችላቸው እንደሚገባ አምባሳደሩ መግለጫቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People Reached
78
Engagements
Distribution Score
Boost Post
75
1 Comment
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.