በደቡብ ክልል 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ አድራጎት ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በክልሉ የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ስራን በዲላ ከተማ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በማደስ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል።
2 ነጥብ 4 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት በጎ አድራጎት ስራው ከ 8 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የክልሉ ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አስቴር ከፍታው ተናግረዋል።
ከተሳፊ ወጣቶቹ 50 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን የገለፁት የቢሮ ሀላፊዋ ከ12 ያህል የስራ መስኮች 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለማዳን መታቀዱን ተናግረዋል።
የበጎ አድራጎት ስራው በበጋ ወቅትም እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!