Fana: At a Speed of Life!

የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ለማበረታታት የመጀመሪያ የሆነ ኮንቬንሽን እየተዘጋጀ ነዉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ለማበረታታትና እዉቅና ለመስጠት የመጀመሪያ የሆነዉን የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ቴክኖሎጂ ኮንቬንሽን በአዲስ አበባ እያዘጋጀ ነዉ፡፡
ኮንቬንሽኑ ከሃምሌ 5 እስከ 8 ቀን 2013ዓ.ም የሚዘጋጅ ሲሆን ÷የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንትና የፕሮፌሰሮች ካዉንስል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማሪያም በእነዚህ ቀናት ስድስት የፓናል ዉይይቶች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አማካሪ ዶክተር አባተ ጌታሁን በዝግጅቱ 57 የመንግስትና የግል ዩንቨርስቲዎችና የምርምርና ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ 51 የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ጨምሮ አንጋፋና ወጣት ሳይንቲስቶች ፣ታዋቂ አገር በቀል እዉቀት አቃቢዎችና ፖሊሲ አዉጪዎች በአጠቃላይ 90 ተቋማት እንደሚሳተፋ ገልፀዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠን ዳይሬክተር ጀኔራል ዶክተር ሰለሞን መኮንን በበኩላቸው÷ ኮንቬንሽኑ “ወደ እዉቀት መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑንና በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡
በዝግጅቱ መጨረሻም የአጋርነት ስምምነትና እዉቅና የሚሰጥ መሆኑንና ዝግጅቱም በየአመቱ የሚቀጥል መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.