Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሶስቱ ሃገራት የትብብር ምንጭ ነው-ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሶስቱ ሃገራት የትብብር ምንጭና ከዚያ በላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት የግብፅና የሱዳን ህዝቦች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያደርስም ገልፀዋል፡፡
የግድቡ ሙሌት በሚካሄድበት ወቅትም ከውሃው ፍሰት ወደ ግድቡ የሚቀር ውሃ ካለም ጥቂት በመሆኑ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የሚደርስ ጉዳት አይኖርም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ግድቡ ተገድቦ ሲጠናቀቅም የአከባቢው ማህበረሰብ የጋራ ብልፅግናን ያረጋግጣል ብለዋል በትዊተር ገፃቸው በአረብኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.