Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል ሰብዓዊ እርዳታ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገለፀ፡፡
መንግስት ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት ከ40 የሚበልጡ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ከተማ የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
ተሽከርካሪዎቹ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎችን የጫኑ ሲሆን÷ የሰብዓዊ ዕርዳታው በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ለተጎዱ ወገኖች እንደሚሰራጭ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.