Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች በእንጦጦ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሰራተኞች በእንጦጦ ከ 3 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚሰሩ ሰራተኞች በእንጦጦ ከ3ሺ በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን እናልብስ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኝው 3ኛው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተሳትፈዋል።
የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩን ያስተባበሩት በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወርቁ ጓንጉል÷ ሰራተኞች ላለፉት ሁለት አመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መሳተፋቸውን አንስተዋል፡፡
ዘንድሮም ኢትዮጵያን በማልበስ ሂደት ውስጥ አሻራቸውን በማኖራቸው ደስታን እንደፈጠረላቸው መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች በአብዛኛው መጽደቃቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው÷ ዘንድሮ የተተከሉት እንዲጸድቁም አስፈላጊውን እንክብካቤ እና ክትትል የጽህፈት ቤቱ ስራተኞች እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.