Fana: At a Speed of Life!

የሞጣ-ጃራጌዶ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 69 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጣ-ጃራጌዶ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 69 በመቶው መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ወደ አስፋልት ንጣፍ ስራ የተሸጋገረ ሲሆን÷ የተራራና የአፈር ቆረጣ ስራዎች የመሬት ጠረጋ ድልዳሎ፣ የሰብ ቤዝ፣ የቤዝ ኮርስ፣ የውሀ ማፋሰሻ መስመር ትቦዎች ቀበራም ተከናውኗል ነው የተባለው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ 58 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በወረዳ 14 ሜትር እና በገጠር 7 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ከአጠቃላይ ስራው ውስጥ 69 በመቶው የሚሆነው ግንባታ የተጠናቀቀው የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሞጣ ከተማ ተነስቶ ጃራጌዶ ከተማ ላይ የሚያበቃ ሲሆን ÷በመንግስት በተመደበ 1 ቢሊየን 640 ሚሊየን ብር በላይ ነው ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው ።
የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ዞሆንግሚ ጄቲኢጂሲ ኮንሶርቲየም የተባለ ዓለም አቀፍ የስራ ተቋራጭ ሲሆን ÷ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እየተከታተለው እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.