ታላቋን ኢትዮጵያ ጃንጥላ አድርገን ህልውናችንን ለማስጠበቅ የሚከፈለውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን – የደቡብ ወሎ ዞን መምሪያ ሰራተኞች
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ታላቋን ኢትዮጵያ ጃንጥላ አድርገን ህልውናችንን ለማስጠበቅ የሚከፈለውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ የደቡብ ወሎ ዞን መምሪያ ሰራተኞች ገለጹ።
ዛሬ ሀምሌ 7 በወቅታዊ የሀገርና የአማራ ክልል ሁኔታ ላይ ውይይት ያደረጉት የደቡብ ወሎ መምሪያ ሰራተኞች ኢትዮጵያዊነትን ጠብቀን በአማራነታችን የተቃጡ ጥቃቶችን ለመመከት ወደኋላ አንልም ብለዋል።
አካባቢያችንን ከመጠበቅ ጀምሮ በህልውናችን ላይ ሥጋት የፈጠረውን ሁሉ ለመከላከል እስከ ህይወት መሥዋዕትነት እንከፍላለን ያሉት ሠራተኞቹ፥ ለአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
የወር ደመወዝ ልገሣውም በአንድ አመት የሚጠቃለል እንደሆነም በውይይቱ ተገልጿል።
የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ መኮነንም የሠራተኞቹን ቁርጠኝነት እና ሀገር ወዳድነት አድንቀው አመስግነዋቸዋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!