የሀረሪ ክልል መስተዳድር የመኝታ አልባሳትን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ክልል መስተዳድር 525 ሺህ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የመኝታ አልባሳትን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ ስነስርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦረዲን በድሪ እና የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ነቢል ዩሱፍ ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባ ገዳዎች እና የተለያዩ የክልሉ ሃላፊዎች ተገኝቷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦረዲን በድሪ በበኩላችው፥ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎኑ ልንቆም የሚገባበት ጊዜ ላይ በመሆናችን መሰል ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የክልሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ነቢል በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፥ መሰል ድጋፎች ካሁን ቀደምም ሲደረጉ መቆየታቸውን አንስተዋል።
በቀጣይም መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሃላፊው ተናግረዋል።
ድጋፉን ያደረገው የሃረሪ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ነው።
በነስሪ ዩሱፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!