በበድር የኢትዮጵያ የሙሰሊሞች ማህበር አማካኝነት ከ500 ሺህ ዶላር በላይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድር የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙሰሊሞች ማህበር እና በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከ500 ሺህ ዶላር በላይ ተሰብስቧል፡፡
ተቀማጭነቱ ዋሽንግተን ዲሲ በሆነው ማህበር እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት “ግድቡ የኔ ነው” በሚል መሪ ቃል የተጀመሪው ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ማሰባሰቢያ የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።
ፕሮግራሙ በተካሄደበት ወቅት በበይነ መረብ ከአምስት መቶ ሃያ ሺህ ዶላር በላይ የተሰባሰበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድጋፉ አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ዶላር ደርሷል።
ይህን ታላቅ አገራዊ አላማ እያስተባበሩ ላሉ የበድር ኢትዮጵያ አመራሮች እና ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች አምባሳደር ፍጹም አረጋ አመስግነዋል።
ሌሎች ማህበራትም ይህን ፈለግ በመከተል በዚህ ታሪካዊ ወቅት ድጋፍ የማሰባሰቡን ዘመቻ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ስለማቅረባቸው የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል፡፡
የባድር ኢትዮጵያ አመራሮችና አባላትም ድጋፉ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንዲሆን እንደሚሰሩ እና በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ለዚህ ስኬት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!