Fana: At a Speed of Life!

ወንጀልና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከል ድርጅቶችና ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነት እንዲያረጋግጡ ፖሊስ አሳሰበ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ ) ወንጀልና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል መኖሪያ ቤት እና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነት እንዲያረጋግጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

በ አዲሰ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነታቸውን ሰውረው መኖሪያ ቤቶችንና መኝታ ቤቶችን በመከራየት ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስለመኖራቸው የፖሊስ የምርመራ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡

የከተማዋን ሠላም በዘላቂነት ማስቀጠል የተቻለው በፀጥታ አካላት ቁርጠኝነት እና በህብረተሰቡ የነቃ ወተሳትፎ መሆኑን የገለፀው ፖሊሰ አሁንም ይህንን ሰላም አሰተማማኝ አድርጎ ማቆየት እንዲቻል ከመቼውም ጊዜ በላይ ለፀጥታ ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት የሚያስፈልግበት ውቅት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልፆ ወንጀል ፈፃሚዎችና ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ምቹ ሁኔታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

ይህንን ለማሳካት በዋናነት የመኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ፤የመኝታአገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣ ፔንሰሊዮኖችና ተመሣሣይ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ቤቶች ማንነታቸው በግልፅ ላልታወቁ ሰዎች ቤት እንዳያከራዩ እንዲሁም በሚያከራዩበት ወቅት የተከራዩን ማንነት የሚገልፁ የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች ሰነዶችን በሚገባ አረጋግጠው በመመዝገብ ይህንንም በየአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው የአዲሰ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የጥፋት ተልኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱና ለአካባቢያቸው እንግዳ የሆኑ ፀጉረ ለውጦች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የፀጥታ አካለት ጥቆማና መረጃ እንዲሰጡ ፖሊስ ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.