ሚኒስቴሩ 453 ሺህ 600 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ከአሜሪካ ተረከበ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር 453 ሺህ 600 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ከአሜሪካ ተረክቧል፡፡
ክትባቱን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።
ክትባቱ የጆ ባይደን አስተዳደር ለኮቫክስ ጥምረት ከሰጠው 25 ሚሊየን ዶዝ የሚጠጋ ክትባት መካከል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የክትባት ስጦታው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ከማሻሻሉ ባለፈ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!