የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛ ዓመት 13ኛው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ምክር ቤቱ በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የቀረበውን የክልሉን የ2014 ዓ.ም በጀት እና በተለያዩ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቷል።
ምክር ቤቱ በቀረበው የክልሉ የ2014 ዓ.ም በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ የ2014 ዓ.ም የሶማሌ ክልል በጀት 29 ቢሊየን ብር እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን ከሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ኤጂንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በቀረቡለት የመንግሥት ባለስልጣናት የሀብት ማስመዝገብ አዋጅ ፣ የክልሉን ኦዲት ቢሮ እንደ አዲስ ለማደራጀት የወጣውን ረቂቅ አዋጅ፣ የስራ ፈጠራ ረቂቅ አዋጅ፣ በክልሉ የደረሱ የሰበዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ፣ ለክልሉ ፍርድ ቤቶች የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ከተወያየ በኋላ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!