Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተሳካ እንዲሆን ዝግጅት ተጠናቋል- የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተሳካ እንዲሆን ዝግጅት አጠናቆ ወደስራ መግባቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።
ይህ የተባለው ቢሮው በምስራቅ አማራ ከሚገኙ ዞኖች ጋር አረንጓዴ አሻራን አስመልክቶ በኮምቦልቻ ከተማ ባደረገው ውይይት ላይ ነው።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ወንድየ ማርቆስ እንደተናገሩት በመርሀ ግብሩ በክልል ደረጃ ለመትከል የታቀደውን 2 ቢሊየን ችግኝ እውን ለማድረግ ሁሉም ዞኖች ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።
በክልሉ የሚገኙ ወረዳዎች ችግኝ የመትከል ስራውን መጀመራቸው የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ወንድየ የፊታችን ሀሙስ በክልል ደረጃ በአንድ ቀን ከ228 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ገልጸው ለዚህም ቢሮው ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል።
በክልሉ ከ18 ሚሊየን በላይ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች መዘጋ ጀታቸው የተገለጸ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም አከባቢዎች ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ ገብተዎል ተብሏል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙ የክልል የዞንና የወረዳ አመራሮች ከውይይቱ ባሻገር በቃሉ ወረዳ 02 ቀበሌ አረንጓዴ አሻራቸውን ችግኝ በመትከል አሳርፈዋል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.