Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የሶሻሊስት ሀገርን በሁሉም ረገድ የመገንባቱን ግብ እናሳካለን- ዢ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናዊ የሶሻሊስት ሀገርን በሁሉም ረገድ የመገንባቱን ግብ እናሳካለን ሲሉ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ገለፁ፡፡
የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ሰሞኑን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አክብሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግን ጨምሮ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ እና የማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን ሊቀመንበር ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ባደረጉት ንግግር “ፓርቲው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የቻይና ህዝብ በኑሯቸው ደስተኛ ማድረግና ታላቅ የመሆን ህልም ተልዕኮው አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
በፓርቲው አመራር ቆራጥነትና በቻይናውያን አንድነት ፣ በሁሉም ብሄሮች መካከል ባለው አንድነት ታላቅ፣ ዘመናዊ የሶሻሊስት ሀገርን በሁሉም ረገድ የመገንባቱን ግብ እናሳካለን ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም የቻይናውያንን ታላቅ የመሆን ህልም እናሟላለን ብለዋል፡፡
ቻይና በመጠኑ የበለፀገ የህብረተሰብን ግንባታ በሁሉም ረገድ አጠናቃለች ነው ያሉት ዢ ጂንፒንግ ይህ ማለት በቻይና የነበረውን ፍፁም የድህነት ችግር ላይ ታሪካዊ መፍትሄ አምጥተናል ማለት ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ዢ በንግግራቸውም ፓርቲው ደም አፋሳሽ ውጊያዎች በመታገል የቻይና ህዝብን በአንድነት እና በማይለዋወጥ ቁርጠኝነት አንድ በማድረግ መርቷልም ነው ያሉት።
በዚህም በሶሻሊዝም አብዮት እና በሀገር ግንባታ በራስ የመተማመን መንፈስ ጠንካራ ቻይናን ለመገንባት ጥረት በማድረግ ታላቅ ስኬትን ማስመዝገብ ችለናል ነው ያሉት።
ፕሬዝዳንት ዢ እንዳሉት በቻይና የኮሚኒዝም ፈር ቀዳጅ ሰዎች ÷ ፓርተውን ሲመሰርቱ እውነትንና ሀሳቦችን ማክበር ፣ ለዋናው ዓላማና ተልእኮ ታማኝ መሆን ፣ መስዋእትነት ሳይፈሩ በጀግንነት መታገል እና ለፓርቲው እና ለቻይና ለህዝብ ታማኝ መሆን በሚለው መርሆ ላይ የመሰረቱት ነው ብለዋል፡፡
የቻይና ህዝብ የትኛውንም የውጭ ኢፍትሃዊ የሆኑ ጫና ዎችንም ሆነ ወረራንበፍጽም አይፈቅድም ብለዋል።
የትኛውም አካል ሙከራዎችን ቢያደርግ ከቻይና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ህዝብ ጋር ይላተማል ም ነው ያሉት ሺ ጂንፒንግ ፡፡
እኛ የትኛውንም ሀገር ባልተገባ መንገድ አንነካም፣አንወርም እንዲሁም በፍጹም ጫናም አናደርግም ብለዋል፡፡
በቀጣይ ጉዟችን ሰላምን፣እድገትን፣ትብብርን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለገለልተኛ የሰላም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንዲሁም ለተረጋጋ እድገት በሚገባ እንዲሆን በሀላፊነት እንሰራለንም ነው ያሉት፡፡
አዲስ አለም አቀፍ ግንኙነት እና የጋራ ነገን የሚፈጥሩ ማህበረሰቦችን ለመፍጠር እንሰራለን ነው ያሉት።
በዚህም ቻይና ጥራት ያለው የቤልትና ሮድ ኢንሼቲቭ በመጠቀም ልማትን በማሳደግ በጋራ ለመስራትና ለዓለም አዳዲስ የልማት እና መልካም እድሎችን ይዛ ትቀርባለች ብለዋል።
“ፓርቲው ከሁሉም ሰላም ወዳድ ሀገራት እና የህዝቦችን ሰላም፣ልማት፣ሚዛናዊነት፣ፍትሃዊነት፣ዲሞክራሲን እና ነጻነትን ከሚያቀንቅኑት ጋር አበክሮ ይሰራል”ሲሉ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.